ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ተሾመ

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድኑን በጊዜያዊነት የሚመሩ አሰልጣኞችን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ቡድኑን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ ከቆዩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ቀጣዩን አሰልጣኝ ለመምረጥ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

በዚሁ መሰረት ኮሚቴው በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እየሰሩ የሚገኙትን ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ቀጣይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከውሳኔ ላይ መድረሱን አመልክቷል።

በተጨማሪ ኮሚቴው ኢንስትራክተር ዳንኤልን እንዲያግዙ በፕሪምየር ሊጉ በመስራት ላይ የሚገኙትና በወቅታዊ ውጤታማነት የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል ያላቸውን የባህር ዳር ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ምክትል አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑን ጠቅሷል።

ፌዴሬሽኑ ለአሰልጣኙ እና ለክለባቸው ባህርዳር ከተማ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃደኛ በመሆናቸው ምክትል አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ገልጿል።

የግብ ጠባቂ አሰልጣኝም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *