ሻሸመኔ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሜር ሊግ አደገ

በሳሙኤል አባተ

በምድብ ለ ሀዋሳ ላይ እየተከናወነ በሚገኜው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ሻሸመኔ ከነማ ቀሪ 4 ጨዋታ እያለው ወደ ቤቲኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል ።

በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 24 አዲስ አበባ ከነማ በቦዲቲ ከነማ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ሻሸመኔ ቀሪ 4 ጨዋታዎች እያሉት በ 47 ነጥብ ፕሪሜር ሊጉን ተቀላቅሏል ።

አዲስ አበባ ከነማ በ35 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በቀጣይ ቀሪ 2 ክለቦች ሊጉን ይቀላቀላሉ ።

በምድብ ሐ  ሀምበርቾ ዱራሜ በ 42 ነጥብ ገላን ከተማ በ 40 ነጥብ የምድቡ አንደኛ ሁኖ ለማለፍ የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል ።

በተመሳሳይ በምድብ ሀ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ 50 ነጥብ ምድቡን ሲመራ ቤንቺ ማጅ በ 47 ነጥብ የምድቡ አንደኛ ሁኖ ለማጠናቀቅ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ቅዱስ ጊዮርጊስ በ48 ነጥብ በአንደኝነት ሲመራ ባህርዳር በ44 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድህን በ38 ነጥብ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ለገጣፎ ለገዳዲ እና ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በእኩል 11 ነጥብ የመጨረሻ ደረጃን ሲይዙ ሲዳማ ቡና ደግሞ 23 ነጥቦችን በመሰብሰብ የወራጅ ቀጠና ውስጥ ያሉ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ናቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *