በሳሙኤል አባተ
በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ዓመታት በኮቪድ -19 ከ7 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጲያ በሶስት ዓመት ውስጥ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው ሲጠቁ ከ7ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።
ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በኮቪድ -19 በሽታ 500 ሺ 774 ሰዎች ሲያዙ ከነዚህም ውስጥ 7ሺህ 574 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል ።
የኮቪድ-19 ክትባት በሶስት ዙር የተሰጠ መሆኑንና የተፈናቀሉ እና እስረኞች የክትባት ተከታታይ ተጠቃሚነት ላይ ቁጥሩ ዝቅተኛ እንደሆነ በጤና ሚኒስቴር የክትባት ኤክስፐርት የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ አየለ ተናግረዋል ።
በዓለም ላይ በኮቪድ -19 በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እንደሚጠቁ የተገለፀ ሲሆን ምክንያቱ እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀ እና ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በተጨማሪ በዓለም ከ685 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲያዙ ስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ የዓለም ጦና ድርጅት መረጃ ያስረዳል።
አሜሪካ፣ ብራዚል እና ህንድ ደግሞ ከዓለማችን ሀገራት ውስጥ ብዙ ዜጎቻቸው በኮቪድ-19 የሞተባቸው ሀገራት ናቸው።