አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተዋል ተብሏል።

የአሰልጣኙን የመልቀቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እየተወያዩበት እንደሆነ ትርታ ስፖርት ዘግቧል።

የስራ አስፈፃሚ አባላቱ በሁለት ሀሳብ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

አንዳንዶቹ አሁኑኑ ይሰናበት ጥያቄውን እንቀበል ያሉ ሲሆን ሌሎች አባላት ደግሞ ቀሪ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ይጨርስ እያሉ ይገኛሉ ተብላል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ከአሰልጣኙ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ውሳኔውን የሚያሳውቅ ይሆናል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ በኮትዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጊኒ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል።

የ45 ዓመቱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የግብጽ ብሔራዊ ቡድንን 2 ለ 0 ማሸነፋቸውን ተከትሎ ብዙ አድናቆት ቢጎርፍላቸውም ያለፉትን ሶስት ጨዋታዎች መሸነፋቸውን ተከትሎ ትችቶን እያየተሰማባቸው ይገኛል።

ኢትዮ ነጋሪ አሰልጣኝ ውበቱ ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ ደብዳቤ ስለማስገባታቸው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ከአሰልጣኑ ለማረጋገጥ ያደረገችው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *