ኢትዮጵያ በ10 ዓመት ከ44 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ከሀገር እንደሸሸባት ተገለጸ

በ10 ዓመቱ ወደ ውጪ ሸሽቷል የተባለው ሀብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ የጥናት ወሬውን የማክሮ ኢኮኖሚ ተንታኝና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ለሸገር ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ተመራማሪው በከተማው ውስጥ ከመደበኛው ሥርዓት ውጪም ከፍተኛ ዶላር እንደሚገላበጥ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ ብቻ 45 ቢሊየን ዶላር በሚዘገንን ሁኔታ ከሀገር ወጥቷል ብለዋል ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ፡፡

በቅርቡ 10 ዓመት የወጣው የውጭ ምንዛሪ ከባለፈው 44 አመት እንደሚልቅ ተሰምቷል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪው በ44 ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያ የሸሸው ሀብት 31 ቢሊየን ዶላር መሆኑን በጥናት ተረጋግጦ መታተሙን ተናግረዋል፡፡

የሀብት ማሸሻ ጥድፊያው በጣም አስደንጋጭ ነው የተባለ ሲሆን ለዚህ የዶላርና የገንዘብ ፍልሰት ወይም ካፒታል ፍላይት ዋነኛው ገፊ ምክንያት በሐገር ውስጥ ያለው የደህንነት ስሜት አለመኖር እና መንግስት በብርቱ ባለመቆጣጠሩ ነው ተብሏል፡፡

በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር አሁንም እንዳይሸሽ መንግስት ቀዳዳዎችን እየደፈነ ከፖሊሲ ባልተናነሰ ችግሮችን እየለየ መሰራት እንዳለበት ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የዶላር ግብይት ሥርዓት ላይ መሰረት የማዕድን አካባቢዎችን ማጥበቅ የኬላ ቁጥጥር ላይ መስራት መፈተሽን እንዲሁም ጥብቅ ህግና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተሰምቷል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *