የ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቀቀ

GERD

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቀቀ

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት  እንዳስታወቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቋል።

የሕዳሴ ግድብ መሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ ዓመትን አስመልክቶ ጽህፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ግድቡ በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን 5200 ሜጋ ዋት ሀይል ያመነጫል።

በ5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ ያለው ይህ የአፍሪካ ግዙፍ ግድብ ወጪው በኢትዮጵያውያን እና በመንግስት በመሸፈን ላይ ይገኛል።

የግድቡ ሁለት ቱርባይኖች አሁን ላይ 700 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት ላይ ሲሆን የግድቡ አራተኛ ዙር ውሀ ሙሌት በመጪው ክረምት ወራት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ግብጽ ኢትዮጵያ በተናጥል በግድቡ ላይ የምትወስደው እርምጃ ታሪካዊ የውሀ ድርሻዬን ይጎዳል በሚል የምትቃወም ሲሆን ኢትዮጵያ በበኩሏ የግድቡ አላማ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት እንደሆነ ተናግራለች።

በኢትዮጵያ 65 ሚሊዮን ዜጎች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ሲሆኑ የህዳሴው ግድብ የሀይል አቅርቦቱን ከእጥፍ በላይ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።
 
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከዚህ በፊት በነበሩ ሶስት ክረምት ወራት ውስጥ በድምሩ 18 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩቢክ ውሀ የያዘ ሲሆን በቀጣዩ ክረምት ደግሞ 24 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሀ እንደሚይዝ ይጠበቃል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *