በወላይታ እናት ከጎረቤቷ ጋር ያላትን የፍቅር ግንኙነት ያወቀ ህጻን በመርዝ ተገደለ
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ በአይጥ መርዝ የተመረዘ በሶ ለልጇ አጠጥታለች የተባለችዉ የ32 ዓመቷ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።
በዞኑ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ቶሚ ገረራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ይህች ሴት ጎረቤቷ ከሆነ አባወራ ጋር በድብቅ የፍቅር ግንኙነት ጀምራለች በሚል የሚወራዉ ወሬ ከ16 አመቱ ታዳጊ ልጇ ጆሮ ይደርሳል።
ልጅም እናቱ ከጎረቤታቸው ጋር የድብቅ ፍቅር ግንኙነት መመስረቷን ተከታትሎ ካረጋገጠ በኋላ በትህትና ሲያዋራት ጥፋቷን አምና ነበር ተብሏል።
ይሁንና የድብቅ ፍቅር ግንኙነቷን ለባሏ እንዳይነግርባት ስጋት የገባት ይህች እናት ልጇን መርዝ አብልታ እንደገደለች ፖሊስ ገልጿል።
እንደ ደቡብ ፖሊስ ምርመራ ከሆነ ይህች እናት ልጇን በድብቅ የጀመረችውን የፍቅር ግንኙነት ለባሏ እንዳይነግርባት በማሰብ እንደገደለችው ለፖሊስ ተናግራለች።