Solar

ህንጻዎች እና ቤቶች በጣሪያቸው ላይ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ እንዲገጥሙ ሊገደዱ ነው

ህንጻዎች እና ቤቶች በጣሪያቸው ላይ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ እንዲገጥሙ ሊገደዱ ነው

በሕንፃዎችና በቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል መጠቀምን አስገዳጅ የሚያደርግ የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ያላትን የፀሐይ ኃይል በሙሉ አቅሟ ለመጠቀም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስቴሩ የኢነርጂ ልማትና መረጃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ዳቢ፣ በሁሉም ሕንፃዎችና ቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል አጠቃቀምን በሒደት አስገዳጅ ለማድረግ የሚያስችል የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ያላትን የፀሐይ ኃይል አቅም የመለየትና በምን መልኩ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚቻል የሚያሳዩ ጥናቶች መጠናቀቃቸውንም አስረድተዋል። ከሌሎች የዓለም ሀገራት ልምድ በመውሰድ፣ በተለይም በከተሞች ረዣዥም ሕንፃዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በእያንዳንዱ ቤትና ሕንፃ ጣሪያ ላይ የፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂን በመግጠም፣ ኃይል የመሰብሰብና ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን…
Read More