Gamonews

በጋሞ ዞን ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 107 መድረሱ ተገለጸ

በጋሞ ዞን ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 107 መድረሱ ተገለጸ

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ፣ካምባ እና ቦንኬ በተባሉ ወረዳዎች በደረሰው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 107 መድረሱን የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ‎ከሟቾቹ መካከል ከጋጮ ባባ ወረዳ ብቻ 102፣ ከካምባ ወረዳ 2 እንዲሁም ከቦንኬ ወረዳ 3 በድምሩ የ107 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስተዳዳሪው ገልጸዋል። አስተዳዳሪው አክለውም እስካሁን በተከናወነው አስቸጋሪ ፍለጋ የ57 ሰዎች አስክሬን መገኘቱንና በጋጮ ባባ ወረዳ የቀሪ 50 ሰዎች አስክሬን እየተፈለገ መሆኑን ተናግረዋል። ‎የአከባቢው መልካምድር አስቸጋሪ መሆን አስክሬን ፍለጋውን ከባድ ማድረጉን የገለፁት የዞኑ አስተዳዳሪው ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት እርዳት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ‎የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በበኩሉ የአደጋ መከታተያ…
Read More