12
Apr
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስር ተመዝግበው ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) እና ከአሜሪካ መንግስት ሌሎች ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል በአገሪቱ ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲያከናውኑ የነበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መረጃቸውን ለመንግስት እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል። ይህ ጥሪ የአሜሪካ አስተዳደር በአገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ እያደረገ ያለውን የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ ወይም ማቆም ጋር በተያያዘ ለቀጣይ ተግባራት አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ይህን ተከትሎም USAIDን ጨምሮ ከማንኛውም የአሜሪካ መንግስት ተቋም የገንዘብ ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማህበር መንግስት በዩኤስኤይድ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቁ ይታወሳል። ባሳለፍነው…