Ethiorika

የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም “ኢቶሪካ” ከወዲሁ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል

የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም “ኢቶሪካ” ከወዲሁ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል

ከስምንት ዓመት ቆይታ በኋላ አምስተኛ አልበሙን እንደሚለቅ ያሳወቀው ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን ወይም ቴዲ አፍሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት ስቧል። የፊታችን ሐሙስ ሚሚያዝያ 8፣2018 "ኢቶሪካ" የተሰኘውን የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች እንደሚያደርስ ካሳወቀ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ዋነኛው መነጋገሪያ ሆኗል። ድምጻዊው ስለ አዲሱ አልበሙ ሊሰጠው ያሰበው ጋዜጣዊ መግለጫ በመንግስት ተጽዕኖ ምክንያት ማካሄድ እንዳልቻለም ተገልጿል። ይህን ተከትሎም ብዙዎች ለድምጻዊው ድጋፋቸው በማሳየት ላይ ሲሆኑ ታዋቂ አርቲስቶች እና የቀድሞ ፖለቲከኞች ድጋፋቸውን ለድምጻዊ ቴድሮስ እያሳዩ ይገኛሉ። ድምጻዊ ቬሮኒክል አዳነ በፌስቡክ ገጿ ላይ ባጋራችው ጽሁፍ "በእውቀትም፣ ዝናን በመቆጣጠርም፣ አለው አለው ባለማለትም፣ በድምፅም፣ ፍቅርን በመስበክም፣ ለህዝብ በመቆምም፣ ሀገር በመውደድም፣ ለተጎዳ በመድረስም፣ ሀይማኖትን በማክበርም፣ ለቤተሰብ ቅድምያ በመስጠትም፣ ታሪክን በማወቅም፣ እግዚአብሔርን…
Read More