20
Aug
ከአንድ ወር በላይ የቆየው የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች እየተወያዩባቸው ካሉ ጉዳዮች መካከል የሰንደቅ አላማ ጉዳይ አንዱ ሲሆን አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለም ባለበት እንዲቀጥል ነገር ግን መሀሉ ላይ ያለው አርማ እንዲቀየር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። ከ8ቱም ቡድኖች በተመረጡ አጠናቃሪዎች የተዋቀረው አዘጋጅ ቡድን እያንዳንዳቸው 500 ሰዎችን ከያዙ 8 ቡድኖች ተቀብሎ ያጣጣማቸውን፣ ድግግሞሽ እንዳይኖር ያስወገደላቸውን የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች አዘጋጅቶ የ8ቱንም ቡድኖች ምክረ ሀሳቦች የያዘ ቃለጉባዔ ለ8ቱም ቡድኖች አቅርቧል። ተመካካካሪዎች በተለያዩ ቡድኖች ተደራጅተው ሀሳብ ከማመንጨት እስከ በሀሳቦቹ መከራከር ድረስ ከመከሩባቸው ስምንት አጀንዳዎች መካከል የሀገር ግንባታ አጀንዳ አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ አጀንዳ በዛሬው ቃለጉባዔ ከተነሱት ምክሮች መካከል የቋንቋ ጉዳዮችተጠቃሽ ናቸው። የቋንቋ ጉዳይን በተመለከተ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ይኑራት?…