23
Apr
የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ሥራ አስኪያጅ ማርክ ሱዝማን ከሚያዚያ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ መሆኑን አስታወቁ፡፡ ስራ አስኪያጁ ለአንድ ሳምንት በሚያደርጉት ጉብኝት በጤና ነክ ተግዳሮቶች ላይ ለመምከርና ለኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የሚቀርፉ እድሎችን ለማመቻቸት ይሠራሉ ተብሏል። ጉብኝቱ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ከመሪዎችና ከማህበረሰቡ ጋር በቅርበት ሆኖ በመሥራት በመላው አፍሪካ ያሉ ዜጎችን ኑሮ መሻሻል የሚያፋጥኑ መፍትሔዎችን ለመደገፍ እያሳየ ያለው ቆራጥነት አካል ነው። በዚህ ጉብኝት ወቅት፤ ሱዝማን የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ ለጋሽ ድርጅቶችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖችን፣ የሳይንስ ሰዎችን፣ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን፣ በቦታው ተገኝተው የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎችንና እና የፈጠራ ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያየ ዘርፍ ላይ ከሚገኙ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል። በነዚህ ውይይቶች ወቅት ሱዝማን አጋሮቻቸው…