ጉናተራራ

በጉና ተራራ ላይ የህዋ ማዕከል የመገንባት እቅድ እንዳለ ተገለጸ

በጉና ተራራ ላይ የህዋ ማዕከል የመገንባት እቅድ እንዳለ ተገለጸ

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በአፄ ቴውድሮስ የተሰየመች ሮኬት ለኹለተኛ ጊዜ ማስወንጨፉ ይታወሳል። ዩንቨርሲቲው በከተማዋ አቅራቢ በሚገኘው የጉና ተራራ ላይ የህዋ ምርምር ማዕከል ለመገንባት እቅድ መያዙን ገልጿል። 154ኛውን የአፄ ቴዎድሮስ ዝክረ-ሰማዕት መታሰቢያ በዓል አስመልክቶ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ትምህርት ዘርፍ በአካባቢያቸው ባለ ቁሳቁስ ከ 2 ኪ.ሜትር በላይ መወንጨፍ የቻለች ሮኬት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ዓመት በፊት አስወንጭፏል። ዩንቨርሲቲው በዚህ ዓመትም በተሻለ መልኩ ማስወንጨፍ መቻላቸውን ዩንቨርሲቲው ገልጿል። የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር አዲሱ ወርቁ እንዳሉት በ2014 የተሰሩት ሮኬትና መድፍ  ዋና አላማ የአጼ ቴዎድሮስን የመቅደላ መድፍን ለመድገምና ኢትዮጽያ ውስጥ የተሳካለት ሮኬትና መድፍ መስራት መቻል እንደሆነ ተናግረዋል።  ሚያዚያ 2014 በሮኬት ሳይንስ ማዕከል አሞራ ገደል ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተወነጨፈችው ሮኬት የት…
Read More