24
May
በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት 70 ዓመት ዳቦ በማቅረብ የሚታወቁት የ'ሸዋ ዳቦ' መሥራቹ ዘሙይ ተክሉ ማረፋቸው ተሰምቷል። የአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ሥያሜውን የተዋሱት የሸዋ ዳቦ መሥራቹ አቶ ዘሙይ ተክሉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል። የኤርትራ መሠረት ያላቸው ዘሙይ ወደ አዲስ አበባ ዘልቀው ያቋቋሙት ሸዋ ዳቦ ለ70 ዓመታት ለአዲስ አበቤዎች ዳቦ ሲያቀርብ ቆይቷል። የአምስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ዘሙይ አንደኛዋ ልጃቸው በአዲስ አበባ ሥማቸው ከሚጠራ ኬክ ቤቶች መካከል የሆነው የ'ቤሎስ ኬክ' ቤት መስራች ሆናለች። በደርግ አስተዳድር ዘመን ለኤርትራ መገንጠል የሚዋጉ አማጽያንን በመደገፍ ታስረው የነበሩት ዘሙይ ተክሉ፣ በከተማዋ የሌላኛው ሥመ ጥር ኬክ ቤት መሥራች የበላይ ተክሉ ወንድምም ናቸው። ሸዋ ዳቦ ቤት በስንዴ መወደድ…