በአዲስ አበባ ለ153 ሺህ ውሾች የእብድ ውሻ ክትባት መስጠት ተጀመረ

የግብርና ሚኒስቴር እንደገለጸው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “የእብድ ውሻ በሽታ” እየተባለ የሚጠራውን በንክሻ እና ቡጭሪያ ወደ ሰዎች የሚተላለፍ በሽታን ለማስቀረት ያለመ ክትባት በመሰጠት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

በሽታው በሰዎች ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ “የውሻ እብደት”በሽታን ለመከላከል 150 ሺህ ውሾችን ለመከተብ ዕቅድ ይዞ እየሰራ እንደሆነም ሚንስቴሩ አስታውቋል።

ከሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም የጀመረው ይህ ዘመቻ ለእንስሳቱ የቤት ለቤት ክትባት መስጠትን አላማ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ ባከናወነው መደበኛ ክትባት ከ100 ሺህ በላይ ውሾችን የከተበ ሲሆን፤ ዘመቻው የውሻ እብደትን ከመከላከል ባለፈ የሰዎችን ደህንነት መጠበቅን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የእንስሳት ጤና መሪ ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ሲሳይ ጌታቸው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባው ዘመቻ እንደተጠናቀቀ፣ የውሻ መክተብ ዘመቻው በሁለተኛ ዙር ወደ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች እንደሚቀጥልም ሚንስቴሩ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ 4 ሺህ 900 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነክሰው የመጡ ሲሆን ምልክት ሳያሳዩ ክትባት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል::ከነዚህ መካከል 1 በመቶ ያህሉ ህክምናውን እንዳቆሙ ገልፀዋል:

በከተማዋ የእብድ ውሻ ህክምና ሚሰጥባቸው ቦታዎች 13 የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ 23 መድረሳቸውን ሲገለጽ ለበሽታው እንደ ችግር የሚታየው ነገር የክትባት መድኃኒቱ ዋጋ ውድ መሆኑ ተጠቅሷል።

ምልክቶቹ ለማሳይት ጥናቶች እንደሚሉት ከሆነ ከሁለት እስከ ሶስት ወር የሚቆይ ሲሆን ነገር ግን እጅላይ ፣እግርላይ እንዲሁም አንገት ላይ መነከሶች በተለይም ለጭንቅላት ቅርብ የሆኑ ቦታዎች ላይ መነከስ ምልክቱ በአፋጣኝ እንዲታይ እንደሚያደርግ እና ከ5 እስከ 20 ቀን ውስጥ ሊታይ እንደሚቻል ተገልጿል።

የእብድ ውሻ በሽታ በየዓመቱ ከ2 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገድል የግብርና ሚኒስቴር ከአንድ ዓመት በፊት ያወጣው ሪፖርት ያስረዳል፡፡

የግብርና ሚንስቴር እንደገለጸው በኢትዮጵያ የእብድ ውሻ በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሳ እና ስጋት እየሆነ በመምጣቱ  በዓመት እስከ 2 ሺህ 7 መቶ የሚደርሱ ሰዎች ይሞታሉ።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *