የጣልያኑ ሊሞንታ ስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ ስታዲየሞችን ለማልማት ድርድር ጀመረ

በዓለም እና ስፔን እግር ኳስ ታሪክ ቀዳሚ የሆነው የሪያል ማድሪድን ስታዲየም ቤርናቢዩ ሜዳ የሰራው ግዙፍ ተቋም በአዲስ አበባ ይገኛል።

ተቀማጭነቱን በጣልያን ያደረገው ሊሞንታ ስፖርት (Limonta Sport) ለስፖርት ሜዳዎች የሚሆኑ ሰው ሰራሽ (Artificial) እና ቅልቅል (Hybrid) ሳሮችን በማምረት እና በማንጠፍ ታዋቂነትን ያተረፈ የስፖርት መሰረተ ልማት ተቋም ነው።

በፊፋ እውቅና ያለው ይህ ተቋም ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል።

ኩባንያው በመላው ዓለም አርቴፊሻል እና ሃይብሪድ የስታዲየም ውስጥ ሳሮችን በማምረት ይታወቃል።

ኩባንያው ከሚያመርታቸው የስታዲየም ውስጥ ሳር መካከል ድብልቁ ወይም ሀይብሪዱ 95 ከመቶው የተፈጥሮ ሳር ሲሆን 5 ከመቶው ደግሞ አርቲፊሻል ሴንቴቲክ ነው ።

ሊሞንታ ኩባንያ የሚያነጥፈው እና የሚያበቅለው ሳሩ በዝናብ ወቅት ውሃን በ5 ደቂቃ ውስጥ የማፍሰስ ችሎታ አለው። ይህ ቴክኖሎጂ በቅርቡ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ 2025 ላይ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል።

ቴክኖሎጂው ከተፈጥሮ ሳር በበለጠ ለረጅም ሰዓት ጨዋታዎችን ማስተናገድ ይችላል የተባለ ሲሆን ለተጫዋቾች ምቹ እና ጉዳትን የሚቀንስ እንደሆነ ይነገርለታል ።

ሪያል ማድሪድ ላለፏት 10 አመታት የሊሞንታን ሃይብሪድ ሳር እየተጠቀመው ሲሆን በአዲስ መልክ የተሰራው ቤርናቡዩንም ሳር ያነጠፈው ይኸው ድርጅት ነው።

ከሪያል ማድሪድ በተጨማሪም ባየር ሙኒክ፣ አያክስ፣ አትሌቲከ ቢልባኦ ፣ ራሽያ አለም ዋንጫን ያስተናገደችበት ጋዝፕሮም ስታዲየም ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።

ሊሞንታ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በአዲስ አበባም የአቃቂ ቃሊቲ ስታዲየም የሳር ጣፍን ለመስራት ሲሆን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየተወያየ ይገኛል።

የከተማው ኮንስትራክሽን እና ግንባታ ቢሮም በውይይቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን ድርድሮቹ እንደቀጠሉ ናቸው።

ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በኋላ የሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ወይም አፍኮን 2029 ለማስተናገድ ለካፍ ጥያቄ አቅርባለች።

ለዚህ ውድድር የስታዲየሞችን ጥራት ለማሳደግ በጥረት ላይ ስትሆን ካፍ በቅርቡ ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።

ፊፋ ባሳለፍነው ሳምንት 62 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ላለው እና በግንባታ ላይ ላለው አደይ አበባ ስታዲየም ሜዳ ጨዋታዎችን እንዲያስተናግድ እውቅና መስጠቱ ይታወሳል።

የባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተመሳሳይ የካፍ እና ፊፋ እውቅና ለማግኘት የተለያዩ የማጠናቀቂያ ስራዎችን በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *