የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በሱዳን ካርቱም ተገደለ

በሱዳን ለ11ኛ ቀን በዘለቀው ጦርነት የሟቾች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል።

ጦርነቱ በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሀይል መካከል ሲሆን አንዱ ባንዱ ላይ ድል መቀዳጀቱ እየተገለጸ ይገኛል።

ጦርነቱ እንዲቆም በርካቶች እያሳሰቡ ቢሆንም ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ ማቆማቸውን ቢናገሩም ጦርነቱ ግን ቆሞ አያውቅም ተብሏል።

የግብጽ መንግሥት እንዳለው በሱዳን ካርቱም የነበራት ወታደራዊ አታቼ መገደሉን አስታውቃለች።

ይሁንና ይህ የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በማን እንደተገደለ እስካሁን አልተገለጸም።

አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሀገራት፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ያስወጡ ሲሆን ቀሪ ዜጎቻቸውን ግን እስካሁን አላስወጡም።

በርካታ ዜጎች በካርቱም ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በኩል አድርገው በመውጣት ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያም በመተማ በኩል ከሱዳን የሚመጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን በመቀበል ላይ መሆኗን ገልጻለች።

አሜሪካ በሱዳን እሚገኙ ዜጎቿን በኢትዮጵያ በኩል አድርጋ ከካርቱም ያስወጣች ሲሆን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ አመስግነዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *