ኢትዮጵያ በሁሉም ወረዳዎች ኢንዱስትሪ የማቋቋም እቅድ እንዳላት ተገልጸ

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ፤ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነግሯል፡፡

እቅዱ በገጠር ያሉ ዜጎች የሚፈልጓቸውን ምርቶች ለመግዛት ወደ ከተማ እንዳይጓዙ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ ያሉ ወረዳዎች በየአካቢያቸው እንደሚያገኙት የግብዓት ዓይነት፤ እያንዳንዳቸው እስከ 3 ኢንዱስትሪዎች እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል፡፡

በዚህም ባለፉት 9 ወራት 206 ኢንዱስትሪዎች በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች መቋቋማቸውን የጠቀሰው ተቋሙ፤ ቁጥራቸውን ለማሳደግ እቀጥላለሁ ብሏል፡፡

በገጠር አካባቢዎች ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት የአካባቢው ነዋሪዎች ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ፤ የስራ እድል በመፍጠር ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ይቀንሳልም ተብሏል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ 151,000 ሰዎች በመካከለኛ እና በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ስራ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል፡፡

የኤልክትሪክ ሀይል በበቂ አለማግኘት፣ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፣ የአስፈፃሚ አካላት አለመናበብ፣ በጥራት ማምረት አለመቻል እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ችግሮች የአምራች ዘርፉን እየፈተኑ ያሉ ችግሮች እንደሆኑም ሀላፊው  ጠቅሰዋል፡፡

ችግሮች ቀንሰው ምርት እንዲጨምር፣ ከሚመለከታቸው ጋር እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በእዚህም ስራ ስራ አቁመው የነበሩ 518  ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪም 2,752 አዳዲስ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ተከፍተዋል መከፈታቸውንም አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል፡፡

በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች በተመረቱ ምርቶች ከዉጪ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ 1.6 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማዳኑንም ገልጸዋል።

እንዲሁም በሀገር ውስጥ ተመርተው ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች ደግሞ 57 ሚሊየን ዶላር የዉጪ ምንዛሪ ገቢ መገኘቱንም ተነግሯል፡፡

ለአምራቾች በ9 ወሩ የተሰጠው የብድር መጠን 6 ቢሊየን ብር መሆኑንና ከዚህ ውስጥም 95 በመቶው መመለስ መቻሉንም ተጠቅሷል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *