ዛሬ ፍጻሜውን ባገኘው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በ2025 በሴቶች ውድድር ትግስት አሰፋ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በወንዶች ደግሞ ኬንያዊው ሴባስቲያን አሸንፏል።
አትሌት ትግስት አሰፋ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን ( 2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች።
ታሪካዊቷ ብሪታንያዊት የማራቶን ሯጭ ፓውላ ራድክሊፍ በሰጠችው አስተያየት አትሌት ትዕግስት አሰፋ ውድድሩን የጨረሰችበትን መንገድ አድንቃ ጀግና አትሌት ነሽ ብላታለች፡፡
አትሌት ትግስት አሰፋ ውድድሯን 2:15:50 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ማጠናቀቋን ተከትሎ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን (2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች።
ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ በውድድሩ ስትጠበቅ የነበረችው ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አተናቃለች።
በተመሳሳይ የወንዶች ማታቶን ውድድር ደግሞ ሰባስቲያን ሳው አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ27 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶባቸዋል።
እንዲሁም ዩጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ሁለተኛ ኪንያዊው አትሌት ሙቲሶ ሙንያኦ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በውድድሩ ተጠብቆ የነበረው እና የፓሪስ ኦሎምፒክ አሸናፊው ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ አምስተኛ ሆኖ አጠናቋል።
በለንደን ማራቶን ውድድር አንደኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ተወዳዳሪ 55 ሺህ ዶላር ሁለተኛ 33 ሺህ እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 22 ሺህ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ፡፡