አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣለች

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ እንዲጣል ያዘዙ ሲሆን ኢትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ተጥሎባታል።

ፕሬዚዳንቱ በነጩ ቤተ መንግሥት በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ እርምጃው አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው።

በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል።

ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከተሞች አበባ፣ ቡና፣ የቆዳ እና አልባሳት ምርቶችን በመላክ ላይ ስትሆን ተጨማሪ 10 በመቶ ቀረጥ ለመክፈል ትገደዳለች።

አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ከ20 በላይ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ከነዚህ ሀገራት አንዷ መሆኗ ተዘግቧል።

በርካታ የዓለማችን ሀገራት ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይተገበራል በተባለው የአሜሪካ አዲስ ቀረጥ ተመን ላይ ንዴታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

የአውሮፓ ህብረት፣ ጀርመን፣ ብሪታንያ፣ ጃፓን እና ሌሎችም ሀገራት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲሱን የታሪፍ አወቃቀር በደስታ እንደምትቀበል አስታውቃለች።

ይህ አወቃቀር የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ አሜሪካ ገበያ ሲገቡ የሚጣልባቸውን ታሪፍ 10% ብቻ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ያሳድጋል ብሏል።

መንግስት ይህ ውሳኔ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና የኢትዮጵያን ኤክስፖርት ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ዉሳኔዉን ተከትሎ እንዳስታወቀዉ ይህ አዲሱ የታሪፍ አወቃቀር ኢትዮጵያ እንደ ቬትናምና ባንግላዴሽ ካሉ ትልልቅ የማምረቻ ማዕከላት ጋር ስትወዳደር የተሻለ እድል እንዲኖራት ያደርጋል።

“የ10% የታሪፍ መጠን ለኢትዮጵያ ላኪዎች ከፍተኛ ማበረታቻ ይሰጣል” ሲል ሚኒስትሩ አስታውቋል ። “ይህ የኢትዮጵያ ምርቶች በአሜሪካ ገበያ ተወዳዳሪ ዋጋ እንዲኖራቸው በማድረግ የፍላጎት እና የኢንቨስትመንት መጨመርን ያመጣል ሲልም ገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *