ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ስለሺ በቀለ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ መልቀቂያ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

አምባሳደር ስለሺ በቀለ  በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ሹመታቸው መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ሌንጮ ባቲ ይተኳቸዋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡

ይሁንና አሜሪካ የአምባሳደር ሌኝጮን ሹመት መቃወሟን ተከትሎ ብናልፍ አንዷለም በዋሸንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡

የቀድሞው የአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ መምህር ስለሺ በቀለ በአምባሳደርነት ከመሾማቸው በፊት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው ከአምስት ዓመት በላይ አገልግለዋል፡፡

አምባሳደር ሽለሺ በታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ በመስጠት የሚታወቁ ሲሆን በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ውይይቶችንም በመምራት ይታወቃሉ፡፡

አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በሳዑዲ አረቢያ አምባሳደርነት የተሾሙት በ2013 አጋማሽ ነበር።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላ በአማካሪነት፣ በኋላ ደግሞ በአምባሳደርነት እያገለገሉ የሚገኙት ሌንጮ ባቲ፣ የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አንደኛው ክንፍ አመራር ነበሩ።

አምባሳደር ሌንጮ በአሜሪካ ለዓመታት የመንግስት ተቃዋሚ ሆነው የኖሪ ሲሆን ከጾታዊ ትንኮሳ ጋር የተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸው ነበር በሚል ወደ ዋሸንግተን ሳይጓዙ ቀርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሁለት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው መሾማቸው አይዘነጋም።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *