ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከ87 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገራት መላኳ ተገለጸ

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸማቸውን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 140 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ለመላክ ታቅዶ ነበር ብለዋል፡፡

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት ዓመት 700 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ለመላክ እቅድ እንደነበረውም ሚኒስትሯ አክለዋል፡፡

ተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት 332 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ መላካቸውም ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የተላከባቸው ሀገራት ስድስት የመካከለኛው ምስራቅ እና ሁለት የአውሮፓ ሀገራት ናቸው። 

ሀገራቱ “የሰለጠኑ” እና “በከፊል የሰለጠኑ” ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ እንደሚፈልጉ የጠቆሙት ሙፈሪያት፤ በጤና፣ በምህንድስና፣ በአርክቴክቸር፣ በሆቴል እና መስተንግዶ ዘርፎች፣ በኤሌክትሪክ እና ቧንቧ ስራዎች እንደዚሁም የጥበቃ ባለሙያዎችን ለመቅጠር ፍላጎቶች እንዳሉ አብራርተዋል።

በጤናው ዘርፍ፤ በህክምና ተቋማት የሚሰማሩ እና በቤት ውስጥ እንክብካቤ የሚያደርጉ ነርሶችን ከኢትዮጵያ የመውሰድ ፍላጎቶች እንዳሉ ሙፈሪያት ገልጸዋል። 

በጤናው እና ምህንድስና ዘርፍ ያሉ ፍላጎቶች ሆኖም ወደ ተግባር ለመቀየር፤ በሀገራቱም እና በኢትዮጵያ በኩል “መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች” እንዳሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

መፈሪያት “መታለፍ የማይችሉ” ሲሉ ከጠቀሷቸው ቅደመ ሁኔታዎች አንዱ፤ ዓለም አቀፍ እውቅና (certification) የማግኘት ጉዳይ ነው።   

ሳውዲ አረቢያ በገፍ ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን በመቅጠር የምትታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሃንዲሶችን፣ አርክቴክቶችን፣ የኤሌክትሪክ እና የቧንቧ ሰራተኞችን የመቅጠር ፍላጎት እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በኳታር እና ኩዌት በሆቴል እና መስተንግዶ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሙያዎችን ለመውሰድ ጥያቄዎች እንደቀረቡም ሚኒስትሯ በሪፖርታቸውን ላይ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በውጭ ሀገራት በስራ ላይ የሚሰማሩት፤ በመንግስት ለመንግስት፣ በመንግስት እና በኩባንያ እንዲሁም በኩባንያ እና ኩባንያ መካከል በሚደረጉ ስምምነቶች አማካኝነት መሆኑንም አክለዋል።

በኢትዮጵያ ከ10 በላይ ስራ አጥ ዜጎች ሲኖሩ ከ100 ሺህ በላይ ደግሞ በየዓመቱ ከዩንቨርሲቲዎች መረቃሉ፡፡

በየዓመቱ ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ 500 ሺህ ዜጎች ወደ አረብ ሀገራት የሚያመሩ ሲሆን ሳውዲ አረቢያ ዋነኛዋ መዳረሻ ሀገር ናት፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *