ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቀረበ

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጩን በይፋ አስጀምሯል፡፡

100 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ሀብት ያለው ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

አንዱን የድርጅቱን አክስዮን ዋጋ በ300 ብር እንደሚሸጥ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም አንድ ግለሰብ መግዛት የሚችለው 33 አክስዮን ወይም 9 ሺህ 900 ብር ነው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮ ቴሌኮም 3 ሺህ 333 አክስዮኖቹን ለሽጭ ያቀረበ ሲሆን 30 ቢሊዮን ብር ከአክስዮን ሽያጭ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች አክስዮን መግዛት ይችላሉ የተባለ ሲሆን ተቋማት ግን አክሲዮንን መግዛት እንደማይችሉ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡

የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃልም ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም 100 ፐርሰን በመንግስት ሀብትነት ተመዝግቦ ለ130 ዓመታት የቆየ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ግን 10 በመቶ ድርሻውን ለመሸጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የአክስዮን ድርሻ ሽያጩን በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን በመግዛት የኢትዮ ቴሌኮም ባለድርሻ እንዲሆኑ ጋብዘዋል።

ስቶክ ማርኬት እንቅስቃሴ ዛሬ በይፋ በኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ሽያጭ መጀመሩንም ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት አሁን ላይ በኢትዮ ቴሌኮም ቢጀምርም ሌሎችም እንደ ስካይ ላይት ያሉ ተቋማት ወደ ስቶክ ማርኬት እንደሚገቡ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ከዛሬ ጀምሮ በቴሌብር መተግበሪያ መግዛት እንደሚቻል የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ እንዲሁም 22 ቢሊዮን ብር ደግሞ የተጣራ ገቢ ማግኘቱ ይታወሳል።

78 ነጥብ 3 ሚሊየን ደንበኞች ያሉት ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው ዓመት ገቢውን ወደ 160 ቢሊዮን ብር ለማሳደግም ማቀዱን አስታውቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *