የድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በ17 ሚሊዮን ብር ተሸጠ

መጠሪያዬ የተሰኘው የድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በኢትዮጵያ ታሪክ ውዱ አልበም ተብሏል

ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበሟ ነሃሴ 23  ለአድማጮች እንደሚደርስ ድምጻዊቷ በዛሬው ዕለት በሰጠችው ጋዜጣዊ  መግለጫ ላይ ተናግራለች።

መጠሪያዬ የሚል ስያሜ ያለው ይህ አዲ የሙዚቃ አልበም  የድምጻዊቷ  የመጀመሪያ አልበሟ ሲሆን  አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቅ 6 ሚሊዮን ብር እንደፈጀባት ተናግራለች፡፡

በመሆኑም የተጠናቀውን  ሙሉ አልበም በ160ሺ የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ17 ሚሊየን ብር በላይ መሸጡን በመግለጫው ለይ ተናግራለች። ይህ ክፍያ በኢትዮጵያ  ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑም ተጠቁሟል።

አልበሙ በተለያዩ  አማራጮች ለአድማጭ የደረሰ ሲሆን ይህም በቴሌግራም ካሴት መተግበሪያ ላይ ፣ በራሷ የዩቲውብ ቻናል እና በዞጃክ  ዓለም አቀፍ  መተግበሪያዎች ላይ እንደሚለቀቅ ተናግራለች።

አልበሙን የገዛው “Zojak worldwide” የተሰኘው የአሜሪካ አሳታሚ ድርጅት ሲሆን በዋናነት የተለያዩ መተግበሪያዎች ላይ የአርቲስቶችን ስራ የሚያከፋፍል ተቋም መሆኑም ተነግሯል።

በአልበሙ ላይ ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ አራት እና  አቡዲ በሰባት ስራዎች በግጥም እና ዜማ የተሳተፉ ሲሆን ሱራፌል የሺጥላ አንድ በስዋህሊኛ የተሰራ ሙዚቃ ሰርቷል።

ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሰለሞን ሃይለማሪያም ሙሉ ሙዚቃውን ራሷ ድምጻዊቷ ፕሮዲውስ ያደረገችው መሆኑ ተነግሯል ።

አልበሙ ነሃሴ 17 ይለቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በህጻን ሄቨን ላይ በደረሰው የአስገድዶ መደፈር ወንጅል እና ሞት ምክንያት  የሚለቀቅበት ቀን ወደ ነሃሴ 23 ቀን መዘዋወሩ ተገልጿል።

ድምጻዊቷ አልበሙ ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመት እንደወሰደባት የገለጸች ሲሆን አልበሙ 12 ትራኮችን ይዟል።

በተጨማሪም ከአልበሙ ላይ  ቅድሚያ ለ2 ዘፈኖች ቪዲዮ በአሜሪካ ሃገር እንደተሰራላቸው እና  አልበሙ በሚለቀቅበትም ቀን በእኩል ሰአት ቪዲዮዎች የሚለቀቁ መሆኑን  በተጨማሪም ግዢው ቪዲዮ ክሊፖችን እንደሚጨምር በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *