አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

ቦብ ሜንድዝ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡

የዘር ሀረጋቸው ከኩባ የሚመዘዘው ሜንድዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋን ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት አገልግለዋል፡፡

እኝህ ጉምቱ ፖለቲከኛ በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አድርገዋል ተብሏል፡፡

እንደ አሜሪካ ድምጽ ዘገባ ከሆነ ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ የነበሩ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ውይይት ወደ ዋሸንግተን እንዲመጣ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

በዋሸንግተን በተደረጉት ተከታታይ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ በጫና ወደ ስምምነት እንድትመጣ ግፊት ሲደረግ እንደነበር እና ኢትዮጵያ ስምምነቱን አልፈርምም በሚል አቋሟ መጽናቷን በወቅቱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ አውጥቶም ነበር፡፡

አሜሪካ ይህን ጫና በኢትዮጵያ ላይ እንድታደርስ እኝህ ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ ከግብጽ ጉቦ በመቀበል በሀገራቸው መንግስት ላይ ጫና አድርሰዋል በሚል በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ፖለቲከኛው እና ባለቤታቸው ናዲስ ሜንደዝ በሌሎች የሙስና ወንጀሎችም ጥፋተኛ እንደሆኑ ሲገለጽ የፊታችን ጥቅምት ወር ላይ ለፍርድ ውሳኔው ተቀጥረዋል፡፡

ምንም አይነት ወንጀል አልሰራሁም የሚሉት ቦብ ሜንደዝ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባላቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ከስልጣን እንዲያገሉ ጫና እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

ከ13 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ስራው ግንባታ የደረሰበት ደረጃ 98 ነጥብ 9 በመቶ ተጠናቋል የተባለ ሲሆን የኤሌክትሮ መካኒካ ስራው ደውም በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ከአፍሪካ ግዙፉ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴው ግድብ በአሁኑ

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *