የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ ኮኮብ ልዊስ ናኒ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

ፖርቹጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ልዊስ ናኒ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ገልጿል፡፡

ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ተጨዋች ሉዊስ ናኒ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ባሰራጨው ቪዲዮ አስታውቋል፡፡

ናኒ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሚመጣው የሰማንያኛ አመት ክብረ በዓሉን በማክበር ላይ ለሚገኘው መቻል እግርኳስ ክለብ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሆን ተገልጿል።

ናኒ ባስተላለፈው አጭር የቪዲዮ መልዕክትም ” ሰላም ኢትዮጵያውያን ሰማንያኛ አመቱን ከሚያከብረው መቻል ግብዣ ስለቀረበልኝ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶኛል።

ለእኔ ልዩ ቦታ ያላትን ኢትዮጵያ ለመጎብኘት ጓጉቻለሁ በቅርቡ እንገናኝ” ሲል ተደምጧል።

መቻል እግር ኳስ ክለብ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር የተቋቋመ ቡድን ሲሆን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተወዳደረ ይገኛል፡፡

ክለቡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በ57 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ በመምራት ላይ ሲሆን ዘንድሮውን ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የማሸነፍ ከፍተኛ ግምት ካላቸው ክለቦች መካከል አንዱ ነው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *