ኢትዮጵያ የሳሞአ ስምምነትን እንድትሰርዝ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በአውሮፓ ኅብረት፣ አፍሪካ፣ ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነትን ውድቅ እንድታደርግ ጠይቋል፡፡

ተቋሙ ይህ ስምምነት የተጠቀሰው የወሲብና የስነ ተዋልዶ ጤና እና መብቶች በሚል ዘርፍ የተደረገው ስምምነት ከግብረሰዶም መብቶች፤ ከፆታ መቀየር፤ ከጽንስ ማቋረጥ እንዲሁም የወሲብ ንግድን የሚያበረታታ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በስምምነቱ የአፍሪካ ፕሮቶኮል አንቀፅ 40.6 ላይ በአህጉሪቱ ለሚገኙ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት የተባለ እጅግ አደገኛ ልቅ የወሲብ ትምህርት እንዲማሩ የሚያስገድድ በመሆኑ እንደሚቃወመውም ገልጿል፡፡

ሌላኛው ተቋሙ የተቃወመው የፆታ ትንኮሳን ማስቀረት በሚል የተቀመጠው ይዘት በጣም አሻሚ የሆነ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ እንዲረዳው በሰነዱ በበርካታ ክፍሎች ውስጥ ” አካታች ” (inclusive) በሚሉ ቃላት ተሸፍኖ እንዲገባ የተደረገ ነውም ተብሏል፡፡

በዚህ የሳሞአ ስምምነት ሰነድ ላይ በርካታ ሥፍራዎች የተጠቀሰው ጾታ የሚለው ቃል ወንድና ሴት ተብሎ እንደሚተረጎም በስምምነቱ በግልጽ ባለመቀመጡ ይልቁንም በርካታ ጾታዎች እንዳሉ በማስመሰል ከኢትዮጵያ ባህል እና ወግ ጋር አብረው የማይሄዱ ሀሳቦች ተካተውበታልም ተብሏል፡፡

ይህ ስምምነት የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን አደጋ ላይ የሚጥሉ አንቀፆችን የያዘ እንደሆነ በባለሙያዎች ጥናት አረጋግጫለሁም ብሏል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት የሳሞአ የንግድና የኢኮኖሚ የአጋርነት ስምምነትን በርካታ ጎጂ ጎኖች እንዳሉት በማመን ከዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ ራሷን እንድታገልል በማድረግ መንግስታዊ ኃላፊነቱንና አደራውን በተግባር እንዲወጣ ጠይቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ኢትዮጵያ የፈረመችውን ይህን ስምምነት እንዳያጸድቅም አሳስቧል፡፡

ይህ ስምምነት ለ20 ዓመት የሚቆይ የጋራ ስምምነት ሲሆን ባሳለፍነው ህዳር ወር ላይ በአውሮፓ፣ አፍሪካ፣ ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመ ስምምነት ነው፡፡

በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ማድረግን በይፋ የከለከለች ሲሆን ባሳለፍነው ነሀሴ ወር ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ የግብረ-ሰዶም መዝናኛ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ፖሊስ እርምጃውን እየወሰደባቸው ያሉት ሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር እንደሆነ ገልጿል።

የተመሳሳይ ጾታ መዝናና ቤቶች ከነባሩ የሀገሪቷ ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ ወንጀሎች ይፈጸምባቸው ነበርም ተብላል።

ፖሊስ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከህብረተሰቡ ጥቆማ እንደደረሰውም አስታውቋል ።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ ናቸው ብሏል። ፖሊስ የተመሳሳይ ጾታ መዝናኛ ቤቶች ባለቤቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየታጣራባቸው

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *