የኢትዮጵያ ገዢ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣናቸው ለቀቁ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሸኘታቸውን ፓርቲያቸው አስታውቋል።
የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ” የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል አቶ ደመቀን በክብር ተሸኝተዋል ” ሲል ገልጿል።
አቶ ደመቀን መኮንንን በመተካት የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
አቶ ደመቀ ከፓርቲው አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች መሆኑ ተነግሯል።
አቶ ደመቀ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታንም ይለቃሉ የሚሉ መረጃዎች ያሉ ቢሆንም እስካሁን የታወቀው በይፋ ከፓርቲያቸው ምክትል ፕሬዜዳንትነት ቦታ መሸኘታቸው ብቻ ነው።
አቶ ደመቀ መኮንን ላለፉት 11 ዓመታት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከሶት ዓመት በፊት ደግሞ አቶ ደጉ አንዳርጋቸውን ተክተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀላፊነትን ይዘው ቆይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ለረጅም ዓመታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት ነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ደርበው የያዙት።
በቀድሞው ኢህአዴግ እና በአሁኑ ብልጽግና ፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሥልጣንን ይዘው የቆዩት አቶ ደመቀ ፤ በብልፅግና ፓርቲ ካሉት ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ ነበሩ።
ጉባኤውን እያካሄደ ያለው ብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የወሰነው ሌላኛው ውሳኔ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ ውይይቶች እንዲቀጥሉ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
ፓርቲው የስብሰባው መጠናቀቅን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ጫና እያሳደሩ ከሚገኙ ጉዳዮች አንዱ “በጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት የተፈጠሩ ትሥሥሮች ያስከተሏቸው አካባቢያዊ ግጭቶች” ናቸው ሲል ገልጿል።
እነዚህን ግጭቶች በመፍታት” የብልፅግና ጉዞን” ይበልጥ ለማፋጠን እና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተሟላ አገራዊ ሠላም ማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ማስቀመጡን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን ወደ ሰላማዊ አማራጭ በማይመጡ የታጠቁ ሀይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው መወሰኑም ተገልጿል፡፡