ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም ተጠየቀች

ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ጥሪ አቀረበ

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ተቋማት፣ በሐማስ የተፈጸመውን ጥቃት እንዲያወግዙ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ አሁን ስለጥቃቱም ይኹን ስለ ግጭቱ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡

ኾኖም፣ ኢትዮጵያ ገለልተኛ አቋም እንዳላትና ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ እንደምትፈልግ፣ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ ትላንት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ሃማስ በእስራኤል ላይ መጠነ ሰፊ  ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን ሰለባ መሆናቸዉን በኢትዮጵያ እስራኤል ኤምባሲ  አስታዉቋል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አደማሱ እንዳሉት በወቅታዊ የጉዳቱን መጠን አሁን ላይ መግለጽ ባይቻልም ከተጎጂዎች መካከል ግን ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡

በጥቃቱ ከ1200 በላይ እስራኤላዉያን መሞታቸዉን አምባሳደር አለሊ አስታዉቀዋል፡፡

በተጨማሪም ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የእስራኤል ጦር ኃይል የሃማስን ጥቃት በመመከት  ጎን ለጎን የሞቱ ዜጎችን እየቀበረ እንደሚገኝ ኤምባሲዉ አስታዉቋል፡፡

ሃማስ የጀመረዉ ጥቃት በቀላሉ የሚታልፍ እንዳልሆነም አምባሳደር አለሊ ገልጸዋል፡፡

እስራኤል አንድ መቶ ሺህ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ማሰመራቷንም አስታዉቃለች፡፡

የሀገሪቱ መከላከያ ሃይልም ከዚህ ጦርነት በኋላ ሃማስ የሚባል የታጠቀ ሃይል  እስከመጨረሻዉ ያሸልባል፤ ከምድረ ገፅም ይጠፋል  እያለ ነዉ፡፡

የእስረኤል ጦር ከሃማስ ወታደሮች ጋር በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል እልህ አስጨራሽ ጦርነት እያካሄዱ መሆኑ እየተነገረ ነዉ፡፡

የጦር ሃይሉ ቃል አቀባይ  ዮናታን ኮንሪከስ በአሁኑ ሰኣት አንድ መቶ ሺህ ተጠባባቂ  ወታደሮችን በደቡባዊ እስራኤል በኩል ወደ ጋዛ እያስጠጋን ነዉ ብለዋል፡፡

‘‘አሁን ስራችን ሁሉ ይሕን ጦርነት በበላይነት ማጠናቀቅ ነዉ ከጦርነቱ ፍጻሜ በኋም ሃማስ የሚሰኘዉ ቡድን እስከመጨረሻዉ ይሸኛል ከዚያ በኋላም ለእስራኤል ስጋት መሆኑ ያካትማል‘‘ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ጦርነት ምክንያት ከሁለቱም ወገኖች ከሁለት ሺህ በላይ ዜጎች መገደላቸዉ ተነግሯል፡፡

በጋዛ ምድር ደግሞ ከ123 ሺህ በላይ ዜጎች ሲፈናቀሉ 100 እስራኤላዊያን ደግሞ በሃማስ  ታግተው ተወስደዋል ተብሏል፡፡

አሜሪካ ደግሞ ለእስራአል አጋርነቷን ለማሳየት የጦር መርከቦቿንና ጄቶቿን ወደ ስፍራዉ እያስጠጋች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሩ ሊዮድ ኦስቲን አስታዉቀዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *