የአፍሪካ ከተማ ከንቲባዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ከነገ ጀምሮ የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሺፕ ኢኒሼቲቭ መድረክ በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እናትአለም መለሰ እንዳሉት ከተማዋ ከነገ ጀምሮ ዓለም አቀፍ፣ አሕጉር አቀፍ እንዲሁም አገር አቀፍ ልዩ ልዩ መድረኮች እንደምታስተናግድ አመልክተዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የአፍሪካ ከንቲባዎች የሊደርሺፕ ኢኒሼቲቭ መድረክ፣ ከ28 እና 29 የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የልህቀት ማዕከልን ለማቋቋም የሚረዳ ዓለም አቀፍ የምክክር መድረክ እንዲሁም ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ መሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረኮች ይካሄዳሉ ብለዋል፡፡

የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አበረታች ውጤት ማስመዝገብ የቻለ መሆኑን በመግለጽ አስተዳደሩ 9 ሺህ 500 ለሚሆኑ ሕጻናትና ወላጆች በከተማዋ አልሚ ምግብ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

መድረኮቹ በሁሉም ረገድ የተጀመሩ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጋራሞች እውቅና እንዲያገኙ ያስችላልም ማለታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የዓለም ከንቲባዎች ጉባኤ ከወራት በፊት በብራዚል የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።
 

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *