የሞስኮ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምሩ ገለጹ

ሩሲያ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ አማርኛ እና ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ትምህርተ ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻ ነበር።

በዚህም መሰረት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስከረም በሞስኮ የሚገኙ ትምህ ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀመራል ሲል የሞስኮ ትምህርት እና ሳይንስ ክፍል አስታውቋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ 1517 የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል ተብሏል።

እንዲሁም 1522 የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል።

ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች።

ሩሲያ በቀጣይም በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻለች።

በመቀጥልም ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ እንደሆነም ከዚህ በፊት ተናግራለች።

ሌላኛዋ የሩቅ ምስራቋ ሀገር ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ማስተማር እንደምትጀምር መግለጿ ይታወሳል።

አማርኛ ቋንቋ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ሆኖ ይሰጣልም ተብሏል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ወደ ቤጂንግ ለጉብኝት ባቀኑበት ወቅት ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት መመረቃቸው አይዘነጋም።

የማስተማሪያ መጽሀፍቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ እንደሆኑ በወቅቱ ተገልጾም ነበር።

የአማርኛ ቋንቋ በጀርመን እና በአሜሪካ ዩንቨርሲቲዎች በመሰጠት ላይ ሲሆን በአሜሪካ በርካታ ግዛቶች የስራ ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስራ ቋንቋ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ባሉ ትምህርት ቤቶች በመሰጠት ላይ ነው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *