ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበሙን በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ ተከለከለ

በኦሮሚኛ እና አማርኛ የሙዚቃ ስራዎቹ የሚታወቀው ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም ለቋል።

“እንዳባቴ እወድሻለሁ” በሚል ለገበያ ያቀረበው ይህ የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም በገበያ ላይ በመሸጥ ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ድምጻዊው በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳለው ምክኒያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ መከልከሉን ገልጿል።

“እንደ አባቴ እወድሻለሁ” የተሰኘዉ አልበም በማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ላይ በይፋ የተለቀቀ ቢሆንም በአዲስ አበባ ሲዲዉን የሚያዞሩ ወጣቶች መሸጥ እንዳይችሉ በፖሊስ መከልከላቸውንም ጠቅሷል።

በትናንትናው እለት ሲዲዉን ለመሸጥ የወጡ ወጣቶች ከተከለከሉ በኋላም ድምፃዊዉ ክልከላዉ ለምን እንደተላለፈ አላዉቅም ብሏል።

ድምፃዊዉ “ሁሉም ሰዉ ለኔ እኩል ነዉ ፤ በእኩልነት በአብሮነት ፣ በአንድነት የማምን ሰዉ ነኝ ያንን ሀሳብ ነዉ በአልበሜ ላይ ለማንጸባረቅ የሞከርኩት” ብሏል።

“ሚዲያ ላይም እንደማይጫወት ጠብቃለሁ” ያለዉ ድምፃዊ አቡሽ ” በዚህ ሞራሌም ሆነ ለኢትዮጵያ ያለኝ አቋም አይቀየርም” ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል።

ድምጻዊ አዲስ አልበሙ ከአቡሽ ዘለቀ የዩቲዩብ ገጽ በተጨማሪ በአይቲዩንስ እና አማዞን ላይ እንደሚገኝም ተናግሯል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ ስላቀረበው ቅሬታ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *