የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የስድስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ

የተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳብን በአብላጫ ድምጽ በ16 ተቃውሞ እና በ12 ድምጽ ተአቅቦ ማጽደቁ ተገልጿል።

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአማራ ክልል እና እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎችም ቦታዎች ተግባራዊ ይሆናል የተባለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጽደቁን ምክር ቤቱ በፌስቡክ ገጹ  አስታውቋል።

የሚንስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል በትጥቅ የተደገፈ እንቅስቃሴ መኖሩን እና ይህንንም በመደበኛው የህግ ስርአት መቆጣጠር የማይቻልበት ሁኔታ መፈጠሩን በመግለጽ ነበር ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወሰነው።

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቦርድ አባላትን እና ሰብሳቢዎችንም መርጧል።

በአማራ ክልል፣ በፌደራል መንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተፈጠው ግጭት ንጹሃን ሰዎች እንዲገደሉ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል።

 ኢሰመኮ ተፋላሚ ሀይሎች ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ለሰላማዊ ንግግር ቦታ እንዲያመቻቹና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታም አሳስቧል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *