የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በቅርቡ የጀመረው አድማስ ድጅታል ሎተሪ የሽልማት መጠኑን ማሳደጉን ገልጿል፡፡
አድማስ ድጅታል ሎተሪ ከመስከረም 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአንደኛ አሸናፊ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በመሸለም ነበር የጀመረው፡፡
በመቀጠልም የሽልማት መጠኑን ወደ ሶስት ሚሊዮን ብር ከፍ የተደረገው አድማስ ድጅታል ሎተሪ ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም በሶስት ብር እና በአምስት ብር የሎተሪ እጣ የሚቆርጡበት የሎተሪ ስርዓት ነው፡፡
በደምበኞች አስተያየት መሰረት ቀደም ሲል የነበበረውን የዕጣ ሽልማት የአንደኛው ዕጣ 4 ሚሊዮን ብር፣ የሁለተኛው ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር የሶስተኛው ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር በማድረግ ተደርጓል ተብሏል፡፡
እንዲሁም ደንበኞች ከሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አንድ እጣ በ10 ብር በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር *127# በመደወል ዕድላቸውን መሞከር እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡
ከ60 ዓመት በፊት ስራ የጀመረው ብሔራዊ ሎተሪ የሎተሪ እድሎችን በቁጥር እና በሽልማት መጠን በየጊዜው እያሳደገ አሁንም ቀጥሏል።
አስተዳድሩ አሁን ላይ 14 አይነት የሎተሪ እድል መሞከሪያ እጣዎች ያሉት ሲሆን ቶምቦላ፣ ዝሆን፣ እንቁጣጣሽ፣ ትንሳኤ፣ የገና ስጦታ፣ ልዩ፣ ቢንጎ፣እና ፈጣን ዋነኞቹ ናቸው።
አሁን ላይ ተቋሙ ከ15 እስከ ሁለት ወራት የሚቆዩ የሎተሪ አሸናፊ እጣዎች ያሉት ሲሆን ለባለ እድለኞች እስከ 20 ሚሊዮን ብር ድረስ በመሸለም ላይ እንደሚገኝ ሰምተናል።
Hi! Do you know if they make any plugins to assist with
SEO? I’m trying to get my blog to rank for some targeted keywords
but I’m not seeing very good success. If you know of any
please share. Thank you! I saw similar art here: Escape room lista