የአዲስ አበባ የ70 ዓመት ባለውለታ አረፉ

በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት 70 ዓመት ዳቦ በማቅረብ የሚታወቁት የ’ሸዋ ዳቦ’ መሥራቹ ዘሙይ ተክሉ ማረፋቸው ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ሥያሜውን የተዋሱት የሸዋ ዳቦ መሥራቹ አቶ ዘሙይ ተክሉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።

የኤርትራ መሠረት ያላቸው ዘሙይ ወደ አዲስ አበባ ዘልቀው ያቋቋሙት ሸዋ ዳቦ ለ70 ዓመታት ለአዲስ አበቤዎች ዳቦ ሲያቀርብ ቆይቷል።

የአምስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ዘሙይ አንደኛዋ ልጃቸው በአዲስ አበባ ሥማቸው ከሚጠራ ኬክ ቤቶች መካከል የሆነው የ’ቤሎስ ኬክ’ ቤት መስራች ሆናለች።

በደርግ አስተዳድር ዘመን ለኤርትራ መገንጠል የሚዋጉ አማጽያንን በመደገፍ ታስረው የነበሩት ዘሙይ ተክሉ፣ በከተማዋ የሌላኛው ሥመ ጥር ኬክ ቤት መሥራች የበላይ ተክሉ ወንድምም ናቸው።

ሸዋ ዳቦ ቤት በስንዴ መወደድ ምክንያት ከሁለት ዓመት በፊስ ስራ ማቆሙ ይታወሳል።

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ታክሲዎች ሸዋ ዳቦ በሚል የሚጠሩ መስመሮች ተሰይሞላቸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *