ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት ያሻሻለችውን የኤክሳይስ ታክስ ህግን ዳግም ማሻሻያ አድርጋለች።
በተቻቻለው ህግ ሙሰረት ከዚህ በፊት ከፍተኛ ግብር የተጣለባቸው ምርቶች ከፍተኛ የሚባል የግብር ቅናሽ ተደርጎባቸዋል።
እንዲሁም ከዚህ በፊት ግብር ያልተጣለባቸው ምርቶች ላይ ጭማሪ ከተደረገባቸቅ ምርቶች መካከል የሞባይል አገልግሎቶች (ኢንተርኔት ፣ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክት)፣ የገመድ አልባ ስልክ አገልግሎት፣ የገመድም ሆነ ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎቶች የ 5 በመቶ ግብር ተጥሎባቸዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ዋጋቸው የቀነሰ ምርቶች ስኳር ለህክምና ከሚውለው በስተቀር የ10 በመቶ ቅናሽ እንደተደረገባቸው ተገልጿል፡፡
ማስቲካ ፣ቸኮሌት እና ጣፋጭ ከረሜላ ምርቶች ከዚህ በፊት 20 በመቶ የኤክሳይስ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩ ሲሆን አሁን የ10 በመቶ ቅናሽ ከተደረገባቸው ምርቶች መካከል ናቸው፡፡
ባህሪው ያልተለወጠ ኢቴል አልኮል ከፍተኛ የግብር ቅነሳ ከተደረገባቸው ምርቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን ከ60 በመቶ ወደ 10 በመቶ ቅናሽ የተደረገበት ምርት ነው ተብሏል፡፡
ሌላኛው የኤክሳይስ ግብር ቅናሽ ከተደረገባቸው ምርቶች መካከል አንዱ ጨው ሲሆን ከ25 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡
የነዳጅ ምርቶችም (ኬሮሲን፣ ቤንዚን፣ እና ናፍጣ) ቅናሽ ከተደረገባቸው ምርቶች መካከል ሌላኛው ሲሆን ከ30 በመቶ ወደ 15 በመቶ ዝቅ እንዲል መደረጉ ተገልጿል፡፡
አልባሳት ምርቶች ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ 8 በመቶ ኤክሳይስ ግብር ተጥሎባቸው የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ተብሏል፡፡
እንዲሁም ምንጣፎች፣ ከጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ የወለል መሸፈኛ ምርቶች ከዚህ በፊት ከነበረበት ወደ 15 በመቶ እንዲቀንስ ሲደረግ ቪድዮ መቅረጫ ወይም ማባዣ መሳሪያዎች፣ የቴሌቪዥን ስርጭት መቀበያዎች ያለምንም ቀረጥ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የተፈቀዱ ምርቶች ናቸው፡፡