በአማራ ክልል ለሶስተኛ ቀን ተቃውሞ ቀጥሏል

በአማራ ክልል ለሶስተኛ ቀን ተቃውሞ ቀጥሏል

የፌደራል መንግሥት የተማከለ የጸጥታ ሀይል ለመመስረት ማቀዱን ተከትሎ የክልል ልዩ ሀይሎች እንዲፈርሱ ውሳኔ አስተላልፏል።

ህጋዊ መሰረት የለውም የሚባለው የክልል ልዩ ሀይል አባላት ወደ ፌደራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ እና መደበኛ ፖሊስ እንዲደራጁም ትግበራ መጀመሩን የፌደራል መንግሥት አስታውቋል።

ይሁንና በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የመንግሥትን ውሳኔ የተጠራጠሩ እና የተቃወሙ ሰዎች ወደ አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተዋል።

በተለይም በሰሜን ወሎ፣ ጎጃም እና ሌሎችም አካባቢዎች መንገዶች በተቃዋሚዎች የተዘጉ ሲሆን ወደ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶችም ተዘግተዋል።

ይህን ተከትሎም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የሚያስኬዱ መንገዶች በከፊል ተዘግተዋል።

ህዝቡ ወደ አደባባይ የወጣው የትግራይ ልዩ ሀይል እና የኦሮሚያ ልዩ ሀይል በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ በሚል ነው።

በተጨማሪም ሁሉም የክልል ልዩ ሀይሎች ትጥቅ ይፍቱ ከተባለ ትግበራው አስቀድሞ በአማራ ክልል መጀመር የለበትም ሲሉም የፌደራል መንግስትን ውሳኔንም ተጠራጥረዋል።

የፌደራል መንግሥት በበኩሉ በአማራ ክልል ልዩ ሀይሉን መልሶ የማደራጀት ስራው እክል እንደገጠመው ገልጾ የአማራ ልዩ ሀይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ የማስፈታት እቅድ እንደሌለው ገልጿል።

የአማራ ክልል መንግስትም የአማራ ህዝብን ጥቅም የሚጎዳ ውሳኔ እንደማይወሰን እና እንደማያስፈጽም አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *