20
May
የመደ ወላቡ ዩንቨርሲቲ 20 መምህራን በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ መምህራኑን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 20 ደርሷል። ዛሬ ረፋድ የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱን ዩንቨርሲቲው አስታውቋል። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ የትራፊክ አደጋ ደርሶባቸዋል። መምህራኑን የጫነው ተሸከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል በመግባቱ በተፈጠረው በዚህ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። ከአደጋው በሕይወት የተረፉት ሌሎች ሰዎች በአደባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢብራሂም…