26
Mar
በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ ላይ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች ባጋጠማቸው የማዕበል አደጋ ምክንያት ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ። " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ትላንት ቅዳሜ ከሰዓት ለኃላ ነው። ባለሞተር ጀልባው የአማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ ቀበሌ ነዋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝ ላይ እያለ በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ማዕበል የመስጠም አደጋው አጋጥማል። በአደጋው የጀልባውን ሹፌር ጨምሮ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። አደጋው መከሰቱ እንደታወቀ የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ ጥረት ቢደረግም በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት አልተሳካም። ከአደጋው መድረስ በኋላ ከአርባ ምንጭ ከተማ በመጡ ዋናተኞች ጭምር ሕይወት ለማዳን ቢሞከርም በሰዓቱ የነበረው ማዕበል አላስቻለም ተብሏል። በጫሞ…