ሿሿ

በቀን 35 ሺህ ብር ይቆጥቡ የነበሩ የሿሿ ሌቦች ተያዙ

በቀን 35 ሺህ ብር ይቆጥቡ የነበሩ የሿሿ ሌቦች ተያዙ

በአዲስ አበባ የ"ሿሿ " ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተለምዶ "ሿሿ "የሚባለውን ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 25 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። ወንጀል ፈፃሚዎቹ ኃይል በመጠቀም ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንበሳ ጋራዥ አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦሮ 86853 ነጭ ሚኒባስ በመጠቀም ከአንድ ግለሰብ ላይ 10ሺ ብርና ግምቱ 14 ሺብር የሚያወጣ ሞባይል ስልክ ሰርቀው ይሰወራሉ፡፡ ፖሊስ ጠንካራ  ክትትል  በማድረግ ወንጀል ፈፃሚዎቹን ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር በማዋልና ምርመራ በማስፋት ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ 14 ወንጀል ፈፃሚዎችንና  የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ኦሮ 79184 ሚኒባስ ተሽከርካሪን…
Read More