የጸጋ በላቸው ጠላፊ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባልደረባ የሆነችውን ጸጋ በላቸው በማገት ወንጀል የተጠረጠረውና ክትትል ሲደረግበት የቆየው ዋና ሳጂን የኋላ መብራት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፤ ግለሰቡ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው ክትትል፤ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በሀገረ ሰላም ወረዳ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጿል።

የጸጥታ ኃይሉ ቀደም ሲል ተበዳይዋን ከጠላፊው ማስጣል መቻሉን ያስታወሰው የሰላምና ጸጥታ ቢሮው፤ በወቅቱ ያመለጠው ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን፤ በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ መቆየቱን ተገልጿል።

በዚህም ተጠርጣሪው አካባቢ በመቀየር ፍለጋውን አስቸጋሪ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተደረገው አሰሳ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተመላክቷል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው ከነበሩ አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና ሽጉጥ ጋር መያዙም ተገልጿል።

ከግንቦት 15/2015 በሐዋሳ ከተማ በተለምዶው አሮጌው መነሃሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጠለፋ የተከናወነባት ጸጋ በላቸው፤ ያለችበት ሳይታወቅ ለ10 ቀናት ያክል መቆየቷ የሚታወቅ ሲሆን፤ ግንቦት 24/2015 ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ መመለሷ ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *