“የአንድ ግጥም አንድ ወግ” ኪነ ጥበባዊ ዝግጅት በድምቀት የተከናወነ ሲሆን በዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተወዳጅ ድራማዎችን እያቀረቡ ያሉት ተዋናዮችና ፕሮዲዩሰሮች የዝግጅቱ ልዩ እንግዶች በመሆን ልምዳቸውን አካፍለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ ” በሀገራችን የኪነ ጥበብና በተለይም በቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ስራዎች ጉልህ አበርክቶ እያከናወነ ካለው ዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን ጋር በትብብር የጥበብ መድረክ ማዘጋጀታችን ወደፊትም ይቀጥላል። ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋርም በትብብር ለመስራት ባሕል ማዕከላችን ክፍት ነው” ሲሉ በመክፈቻ ዝግጅቱ ወቅት ተናግረዋል።

የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ኃላፊ ወ/ሮ ትህትና ተስፋዬ በበኩላቸው ” እኔ እና ዲኤስቲቪ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የብራንድ ትውውቅ ከ አአዩ ባሕል ማዕከል ጋር መዘጋጀቱን ገልፀው አብዛኛው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተመልካች ከስፖርት እስከ ፊልም በዲኤስቲቪ የማይረሱ ትዝታዎችን በማይደገሙ አጋጣሚዎች ያሳለፈው ትዝታ ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል።
የማርኬቲንግ ኃላፊዋ “ዲኤስቲቪ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመዝናኛ አማራጮችን እያስፋፋ የተለያዩ አማራጭ ያላቸው ስድስት ፓኬጆችን ጎጆ፣ ቤተሰብ ፣ ሜዳ፣ ሜዳ ስፖርት፣ ሜዳ ፕላስ እና ፕሪምየም በተሰኙ አማራጮች በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ነው” ብለዋል።
በተለይም DStv “ጎጆ” የተሰኘው ፓኬጅ የበርካታ ደንበኞችን ኪስ የማይጎዳ ጥሩ ምርጫ እና በሀገርኛ ቋንቋ ተከታታይ ድራማዎች፣ የልጆች መዝናኛዎችና የተመረጡ የስፖርት ፕሮግራሞችን እያቀረበ ያለ አማራጭ ነው።
አቦል ቲቪን ጨምሮ ኒክ ጁኒየር በአማርኛ፣ Maaddii Abol፣ ZeeAlem፣ Nat Geo ቻናሎችን እና ሌሎችን ያካተተ አማራጭ መሆኑን አውስተዋል።
ወ/ሮ ትህትና ለኢትዮጵያውያን እግር ኳስ አፍቃሪዎች በልዩ ሁኔታ የቀረበውንና ገና አንድ ዓመት የሆነውን ” ሜዳ ስፖርት” ፓኬጅን በተመለከተ በአፅንኦት ያብራሩ ሲሆን በሱፐርስፖርት ቻናሎች ላይ የሚተላለፉትን ሁሉንም የእግር ኳስ ወይንም የሊግ ጨዋታዎችን፣ በዋናነት ደግሞ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ተመልካቾችን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ፓኬጅ ነው። ይህ ፓኬጅ ለእኛ አገር ብቻ በልዩ ሁኔታ የቀረበ እና ዋጋውም ቀድሞ ቻምፒዮንስ ሊግ ይታይበት ከነበረው የ “ሜዳ ፕላስ ፓኬጅ” ዋጋ ቅናሽ ተደርጎበት የተዘጋጀ ነው” ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን እግር ኳስ አፍቃሪያንም የዚህ ” ሜዳ ስፖርት ” ፓኬጅ ተጠቃሚ ቢሆኑ እርካታ ያገኛሉ ሲሉ መክረዋል።
በዕለቱ የመድረክ እንግዶች የነበሩትና የዲኤስቲቪ አቦል ተከታታይ ድራማ አዘጋጆችና ተዋናዮች በበኩላቸው በአቦል ቻናል የ“ኮሚሽኒንግ” እና የ“ላይሰንሲንግ” የፋይናንስ ትብብር ሥርዓት ያላቸውን ሃሳብና ተሰጥኦ በላቀ የፕሮዳክሽን ጥራት ስራዎቻቸውን ለእይታ ለማብቃት ያገኙትን ጥሩ አጋጣሚና ልምድ አካፍለዋል።
በመድረኩ አቦል ቴሌቪዥን የፊልም ባለሙያዎች ፋይናንስ ላይ ሳይጨነቁ በፕሮዳክሽኑ ጥራት ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ እስከዚህ ዓመት ድረስ ከ125 በላይ የፕሮዳክሽን ኩባንያዎች ጋር መስራቱ ተገልጿል።
ዲኤስቲቪ ለባለሙያዎች በሚያደርገው ድጋፍና ሙያዊ ስልጠና የፕሮዳክክሽን ጥራት ከሌሎች የዲኤስቲቪ ኤም-ኔት አቻ ቻናሎች አንፃር ተዋዳዳሪ ሆነው እንዲዘጋጁ የምስል ጥራት፣ የድምጽ ጥራትና የታሪክ ነገራ ጥራት መሻሻሎች እንዲመዘገቡ ያደረገው አስተዋፅኦም ተጠቅሷል።
ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኢንዱስትሪም ዕለታዊ ተከታታይ ድራማን ጨምሮ “ሚኒ ድራማዎችን” ማስተዋወቁም በበጎ አስተዋፅኦ ተገልጿል።
በመልቲቾይስ አካዳሚ አማካኝነትም ወጣት የፊልም ባለሙያዎች የአንድ ዓመት የፊልም ጥበብ ስኮላርሽፕ፣ እንዲሁም ለአንጋፋ ባለሙያዎች ደግሞ የማስተርክላስ ስልጠናና ወርክሾፖችን በአካልና በኦንላይን እያቀረበ ስለመሆኑም በዝግጅቱ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የዲጅታል ስትሪሚንግን በማስፋፋት ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የ “ዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል” ይፋ መደረጉ በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን የኢትዮ ቴሌኮምን የፊክስድ ብሮድባንድና የሞባይል ኢንተርኔት ዳታ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከጠበቁት የዲኤስቲቪ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች ጋር ያዋሃደና እንደ ማዕድ በአንድ ገበታ የቀረበ መሆኑም ተገልጿል።
ደንበኞችም የስትሪሚንግ አገልግሎቱን በመመዝገብ ብቻ ዲሽና ዲኮደር ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ መጠቀም ያስችላቸዋል የተባለ ሲሆን በፈለጉት የስማርት ዲቫይስ ( ስልክ፣ ታብሌት፣ ላፕቶብና ቴሌቪዥን ) ቦታና ሁኔታ ሳይገድባቸው የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶችን መመልከት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯልም ተብሏል።
በዝግጅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትርና ፊልም ጥበብ ተማሪዎች በአቦል ቴሌቪዥን የተላለፉና እየተላለፉ ካሉ ተወዳጅ ድራማዎች ቅንጭብ የገጸ ባሕሪያት ትወና ውድድር ያከናወኑ ሲሆን ለአሸናፊዎችም የዲኤስቲቪ ስትሪም ልዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።