በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ83 ሺህ በላይ  ሰዎች በካንሰር ምክንያት ይሞታሉ ተባለ

በኢትዮጵያ  የካንሰር ታማሚዎች ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱት የህመሙ ደረጃ ሶስት እና አራት ከደረሰ በኋላ መሆኑ ተገልጿ።

ይህንን ለማዳን ከባድ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑም በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ሌሊሳ አማኑኤል ተናግረዋል። 

የካንሰር ህመም  ቀድሞ ማከም እና መከታተል ከተቻለ መዳን የሚቻል ህመም መሆኑን አማካሪው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛ መምጣቱን እና በዓመት ከ83 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሰር በሽታ እንደሚያዙም አክለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት 19 ሚሊዮን ሰዎች በካንሰር የሚያዙ ሲሆን 10 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተነግሯል።

ከእነዚህም መካካል 75 በመቶ የሚሆነው  ዝቅተኛ የሆነ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሀገራት ላይ የሚከሰት መሆኑ ተገልጿል ።

በሌላ በኩል የህጻናት የካንሰር ህመም በተመለከተ በዓመት 400 ሺህ የሚሆኑ የሚያዙ ሲሆን 90 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባለቸው ሀገራት ላይ የሚከሰት እንደሆነ በጤና ሚኒስትር በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር አስተባባሪ የሆኑት ሲስተር ታከለች ሞገስ ተናግረዋል።

በርካታ ህጻናት በካንሰር ህይወታቸው የሚያልፍ ቢሆንም ከአዋቂ አንጻር የህጻናት የካንሰር ህመም ማዳን የሚቻልበት መጠን ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።

በዚሁ ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው የበልሻ ፋውንዴሽን የካንሰር በሽታን የመከላከል ስራ መስራት ፣ ህሙማን የህክምና አገልግሎት እና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ፣ በካንሰር እና በሌሎች  ምክንያቶች  ወላጅ አልባ የሆኑ እና ለችግር የተጋለጡ ህጻናት ለመደገፍ  ዓላማው አድርጎ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን የበልሻ ፋውንዴሽን መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አበበ መብራቴ ገልጸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *