ኢትዮ ቴሌኮም የ10 ሚሊዮን አክስዮን መሸጡን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ከ47 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ባለድርሻ መሆናቸውን ገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሽያጭ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በማስጀመር የአክሲዮን ሽያጩን እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

በመቀጠልም ውጤቱን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እና ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣንበማቅረብ እና በመገምገም በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሽያጭ ቀነ-ገደቡን በማራዘም እስከ የካቲት7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማለትም ለ121 ቀናት በዲጂታል መንገድ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት የተከናወነው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ ውጤት በየደረጃው በሚገኙየመንግስት አካላት ተገምግሞ እንዲሁም በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታይቶ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡

ከ47 ሺህ በላይ ዜጎችን በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያስችል ወሳኝ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ሲል ድርጅቱ ገልጿል።

በአክሲዮን ሽያጩ ወቅት በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ተቋማት እና ውጪ የሚኖሩ ባለሀብቶች ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ያሳዩ ቢሆንም በቅድሚያ በሀገር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊነት ለማረጋገጥ ታሳቢ በማድረግ ለዜጎች ዝቅተኛ መሸጫ ዋጋ በማስቀመጥ ሲከናወን ቆይቷል ብሏል።

በተለይም ኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ ለሽያጭ በማቅረብ ዜጎች በመተማመን ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማስቻል በቀጣይም አክሲዮናቸውን ማንቀሳቀስ ወደ ሚችሉበት የሰነደ መዋዕለ ንዋይ (Stock Market) ልምምድ በመግባት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካለ ፍላጎት የመነጨ ነው፡፡

በዚህም መሰረት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች በስፋት በመሳተፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአጠቃላይ ከ47,377 ዜጎች ከ10.7 ሚሊዮን የኢትዮ ቴሌኮም መደበኛ አክሲዮኖች የግዢ በዲጂታል መንገድ በማከናወን ብር 3.2 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብት ለማሰባሰብ ተችሏል፡፡

በቀጣይ ከእያንዳንዱ አመልካችጋር በሚኖር የቀጥታ ግንኙነት ያልተሟሉ መረጃዎችን የማሟላት ተግባር በማከናወን የተቋማችን ባለቤት የሚሆኑበት ማረጋገጫ የመስጠት ስራ ይከናወናል ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የተሸጡ አክሲዮኖች ድልድል በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የማጽደቅ ሂደት ከተከናወነ በኋላ ውጤቱን በይፋ አሳውቃለሁም ብሏል።

የተደለደሉ አክሲዮኖች በማዕከላዊ የሰነዶች ሙዓለ ነዋዮች ግምጃ ቤት ይመዘገባሉ፤ ይህም ሂደት እስኪጠናቀቅ ኢትዮ ቴሌኮም መረጃዎችን ለባለአክሲዮኖች ደረጃ በደረጃ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ባለድርሻ የሚሆኑ ባለአክስዮኖች በቀጣይ በኢትዮጵያ የሰነዶች ሙዓለ ነዋዮች ገበያ አክስዮናቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተቋማችንን በገበያው እንዲመዘገብ ቀጣይ ስራዎች ይከናወናሉም ብሏል።

ቀሪ አክስዮኖች በተመለከተ ዝርዝር የሽያጭ ሂደቱን በቀጣይ አሳውቃለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም አሁን አክሲዮን የገዙ ባለድርሻዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ይሁንታ በማግኘት በድጋሚ ለገበያ እንደሚቀርቡ አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *