ቴክኖ ሞባይል የቴክኖ ኤአይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋውቋል፡፡
ቴክኖ ሞባይል በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀው የቴክኖ ኤአይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል፡፡
አዲሱ የቴክኖ ኤአይ (Tecno AI) አጋዥ ቴክ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመስራት የሚያስችል አጋዥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ተካቶለታል ተብሏል፡፡
የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊክ “ቴክኖ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ጉልህ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝ” ጠቅሰዋል።
አቶ አሊክ “ቴክኖ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እንዲሁም ማህበረሰቡ አለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመድ መትጋቱን እንደሚቀጥል” አረጋግጠዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ስለ ፋንተም V2 የታጣፊ ስልኮች ከቴክኖ ኤአይ ጋር አጣምረው ስለመጡት ቴክኖሎጂ በምስል የታገዘ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ከኤአይ ቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ እንደ VR ያሉ የኤይአይ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጌሞች ላይ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በተጨማሪም የስልኮቹን የካሜራ ብቃት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽንም ለዕይታ ቀርቧል፡፡
ቴክኖ ሞባይል ከአለም የቴክኖሎጂ ገበያ ጋር ተወዳዳሪ የሆኑ እና ከፍ ያለ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ወደ ተጠቃሚ ማድረሱን ቀጥያለሁ ብሏል።
ቴክኖ ሞባይል በአዲስ አበባ ከተማ ጎሮ አይሲቲ ፓርክ ባስገነባው ፋብሪካ የሚገጥማቸውን ዘመናዊ የሞባይል ስልኮች ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት በመላክ ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ መሆኑንም ተናግሯል፡፡