የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ጣቢያ ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል።
በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው አውሮፕላን ጣቢያ በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚገነባ ገልጿል።
ይህ አውሮፕላን ጣቢያ ወይም ኤርፖርት የሚገነባው በዓመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን ብቻ የማስተናገድ ያለው ቦሌ ዓከም አቀፍ ኤርፖርትን ለመተካት እንደሆነ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
በቢሾፍቱ ልዩ ስሙ አቡ ሴራ በተባለው ስፍራ የሚገነባው ይህ ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን ዳር የተሰኘው ኩባንያ መመረጡንም አቶ መስፍን ገልጸዋል።
አቶ መስፍን አክለውም አዲሱ ኤርፖርት ግንባታ በአምስት ዓመታት ውስጥ በሁለት ዙር ይገነባል ያሉ ሲሆን ለመጀመሪያው ዙር ግንባታ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደርግበታልም ብለዋል።
ኤርፖርቱ ባንድ ጊዜ አራት አውሮፕላኖችን የማሳረፍ እና መንደርደሪያ መም ይኖረዋል ተብሏል።
270 አውሮፕላኖችን የማሳረፍ አቅም ያለው አዲሱ ኤርፖርት ከቦሌ ኤርፖርት ጋር የሚያስተሳስር ፈጣን ባቡር እና መንገድ እንደሚገነባ ተገልጿል።
ለአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ የሚያስፈልገው ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በብድር እንደሚሸፈን የተገለጸ ሲሆን ብድር ለመስጠት የሚፈልጉ ተቋማት መገኘታቸውንም አቶ መስፍን ተናግረዋል።
ይሁንና የአዲሱን ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን የሚሰራው ዳር ኩባንያ ወጪ ምን ያህል እንደሆነ አቶ መስፍን ከማገር ተቆጥበዋል።
Aw, this was a really good post. Taking a few minutes and actual effort to
produce a top notch article… but what can I say… I put things off
a whole lot and don’t seem to get anything done.