በታሸገ ውሃ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግ ነው

የታሸገ ውሃ አምራቾች በሦስት ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የታሸገ ውሃ አምራቾች ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ መወሰናቸውን ገልጸዋል።

አዲስ በሚጠበቀው የታሸገ ውሃ የማከፋፈያ ዋጋ ጭማሪ በሁለት ሊትር ውሃ ላይ እስከ 20 በመቶ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ይህም በሶት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የውሃ አምራቾቹ በኅዳር ወር በተመሳሳይ የ22.5 በመቶ ጭማሪ አድርገው የነበረ ሲሆን በወቅቱ ለዋጋ ማስተካከያው ምክንያት ነው የተባለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና ሌሎች ግብአቶች ወጪያቸው ጨምሯል በሚል ነበር።

በቀጣይ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ጭማሪ ምክንያታዊነቱ ላይ ጥያቄ ያስነሳል የተባለ ሲሆን የዋጋ ጭማሪው በተጠቃሚዎች እና አከፋፋዮች ላይ እክል ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል ሲል ካፒታል ዘግቧል፡፡

በአዲሱ ጭማሪ መሠረት 6 ፍሬ የሚይዘው ባለ ሁለት ሊትር ውሃ አሁን ካለበት 125 ብር ለአከፋፋይ ማስረከቢያ ዋጋ ወደ 150 ብር ከፍ ሊል እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

ቸርቻሪዎች ደግሞ በ150 ብር የተረከቡትን ተመሳሳይ ምርት ወደ 170 ብር ከፍ ሊያደርጉት እንደሚችሉም ይጠበቃል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *