ካሊፎርኒያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 102 የዲጂታል ማርኬቲንግ  ሰልጣኞቹን አስመረቀ

ከሁለት ዓመት በፊት በዲጂታል ስልጠናዎች ዘርፍ የተሰማራው ካሊፎርኒያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአጫጭር ስልጠናዎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ድርጅቱ ከሚጣቸው ስልጠናዎች መካከልም በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ ዌብሳይት ማበልጸግ፣ ኮዲንግ፣ግራፊክ ዲዛይኒንግ እና ተዛማጅ ሙያዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡

መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀት ካላቸው ፣ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የሚችሉ ሰዎች ማንኛውም ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉ ሰዎች ስልጠናውን ማግኘት እንደሚችሉም የኢንስቲትዩቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል አሰፋ በምረቃው ወቅት ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ  ለአንድ ወር  ተኩል የተግባር ትምህርትን ጨምሮ  የተለያዩ መሰረታዊ ስልጠናዎችን አግኝተዋል። 

ከተመራቂዎቹ  ውስጥ   ከግማሽ በላይ  ወንዶች ሲሆኑ  የዛሬ ተመራቂዎቹ   ሁለተኛ ዙር ተመራቂዎቹ ናቸው።

በዲጂታል ማርኬቲንግ  ኢንተርኔትን በመጠቀም  በሞባይል ስልክ  ፣ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ ዌብናሮችን፣ በሰርች ኤንጅ ሌሎች ዲጂታል መድረኮችን  በመጠቀም የዛሬ ተመራቂዎች ምርትና አገልግሎት ማስተዋወቅ መሸጥ ማሻሻጥ  ላይ ሰፊ ስራዎች ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ድርጅቱ ለምን ስሙን ካሊፎርኒያ ትሬኒንግ ኢንስቲትዩት አላችሁት በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄም የዓለማችን ዋና ዋናዎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መነሻቸው ካሊፎርኒያ በመሆኑ እኛም ስሙን በዚህ ልንጠራው ችለናልም ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የድጅታል ማርኬቲንግ ሙያ ገና በመጀመር ላይ ነው ያሉት አቶ ሱራፌል ካሊፎርኒያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዘርፉ እንዲያድግ የሚችለውን አስተዋጽኦ ያበረክታልም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ እና በበይነ መረብ የታገዙ ለማድረግ ድጅታል ኢትዮጵያ የተሰኘ የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጅታ በመተግበር ላይ ትገኛለች፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *