የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ብራዛቪል በረራ የጀመረበትን 40ኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኮንጎ ዋና ከተማ ብራዛቪል የቀጥታ በረራ የጀመረበትን ዓመት አክብሯል፡፡

በአፍሪካ ከተመሰረተ ረጅም ዓመት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 1983 ላይ የመጀመሪያውን የቀጥታ በረራ ወደ ብራዛቪል አድርጎ ነበር፡፡

አሁን ላይ አየር መንገዱ በሳምንት 10 በረራዎችን ከአዲስ አበባ-ብራዛቪል የደርሶ መልስ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ከ63 በላይ ከተሞች በመብረር ላይ ሲሆን ይህም ከየትኛውም የዓለማችን አየር መንገዶች በላይ በአፍሪካ ሰማይ ላይ የሚበር አየር መንገድ አድርጎታል፡፡

በታህሳስ 1945 የተመሰረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያ በረራውን ወደ ግብጽ ካይሮ አድርጓል፡፡

የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዱባዩ ኤርሾው ላይ ተገኝተው እንዳሉት አየር መንገዱ ከቦይንግ እና ኤርባስ 78 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማምተዋል፡፡

በ2022 ለ13 ሚሊዮን ዜጎች የበረራ መስተንግዶ የሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ አሁን ላይ 145 አውሮፕላኖች እንዳሉት የገለጹት ስራ አስፈጻሚው የ2035 እቅዱን ለማሳካትም ተጨማሪ 130 አውሮፕላኖችን መግዛት እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *